በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው በመጀመሪያ ዙሮች ያልተሳኩ የለያዩ ዕቃዎች ግዥ ማለትም

ሎት 1 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ሎት-2 የተለያዩ ፈርኒቸሮች የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር የሚችሉት ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባቸዉ መስፈርት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ሰርትፍኬት የአቅራቢነት ሰርትፍኬት የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በቢድ ቦንድ በግዥ መመሪያ ላይ ከተፈቀዱ ዘዴዎች በአንደኛው በባንክ የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ በ200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። የዕቃ የጥራት ጉድለት በሚታይበት ግዜ አቅራቢው ወዲያውኑ የማስተካከልና የመቀየር ኃላፊነት አለበት።

ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን ስሞሉ ሰነዱን ያለሥርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት በሁሉም ገጽ ላይ በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በፖስታ ታሽጎ በፖስታው ላይም የጨረታው ዓይነት ስልክና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በዕለቱ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፤ ጨረታውን ያሸነፈ አካል ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመግባት ጥራቱንና ወቅታዊነቱ የጠበቀው ዕቃ እስከ መ/ቤታችን ድረስ የትራንስፖርትና የአውራጅ ወጭውን ችሎ በማምጣት ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።

ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ይከፈታል። 16ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሲቀር በሚቀጥለዉ ሥራ ቀን ሂደቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ማሳሰቢያ፡- በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግዎን ያረጋግጡ

ስልክ 09 83 26 16 48/ 046-181 4091

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ

ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Publishing entity: የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders