በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት አጥር ግንባታ እና የቢሮ ህንጻ ጥገና ለማካሄድ በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

Description

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት አጥር ግንባታ እና የቢሮ ህንጻ ጥገና ለማካሄድ በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ፡-

  1. GC 6/B C 5 እና ከዚያ በላይ
  2. በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡና በ2018 ዓ.ም. የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላያሱ
  3. ከመንግሥት የሚፈለግበት የግብር እና የታከለ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዓመቱ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከታክስ አስተዳደር ቢሮ እና አቻ ተቋም ማቅረብ የሚችል
  4. ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
  • በክልሉ እና በዞን የግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ስራ አፈጻጸም ያላቸውና ስራዎችን ያላስተጓጎሉ እና ውል ያላቋረጡ ተቋራጮችን እየጋበዘ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተቋራጮች የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር / በኘሮጀክቱ ስም በኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዘው በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶቻቸውን በመሙላት ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አድርጎ በኤንቨሎፕ በማሸግ በእያንዳንዱ ላይ ማህተሙንና ፊርማውን በማሳረፍ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 21 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ጨረታው የሚከፈተው የመጨረሻ ቀን ሆኖ የጨረታው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ለሁሉም እንዲመች ዕለተ ሰኞ ከ4፡00 ሠዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት ይከፈታል። ለተሸነፉት ተጫራቾች ወድያውኑ ያስገቡትን ሲፒኦ/CPO ይመለስላቸዋል።
  • በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፍ ይኖርበታል። እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ / CPO/ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለ 90 ቀን ማቅረብ ይኖርበታል ። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጪ ይደረጋሉ።
  • ጨረታው የሚዘጋው በ21ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው ህጋዊተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 ይሆናል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ የሚቀርብ የሥራ ተቋራጭ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
  • የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የማብራሪያ ግድፈት ካለው የጨረታ ዶክመንት የበላይነት ይኖረዋል።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ሰ.ቁ 09 16 42 82 42/ 09 16 95 99 41 ይደዉሉልን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ጌዴኦ ዞን

የኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-18
  • Publishing entity: በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 28, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders