የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የስፖርት ምክር ቤት ተጠቃሚ ለሆኑ የመ/ቤቱ የሠራተኞች የስፖርት ትጥቅና ግብዓት ግዥዎችን በምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 004/2018

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የስፖርት ምክር ቤት ተጠቃሚ ለሆኑ የመ/ቤቱ የሠራተኞች የስፖርት ትጥቅና ግብዓት ግዥዎችን በምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፦

ሎት 1 የስፖርት ትጥቅና ግብዓት

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፣ ቲን ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱ በኢንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰናድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሰት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. ጨረታው እስከ ከ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በሎት1 የስፖርት ትጥቅና ግብዓት ለተጠቀሰው 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ከአዳራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ፑል የመንግሰት ግዥ ቡድን ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል።
  7. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ሎትı በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ናሙና ማቅረብ /ግዴታ ወደ ጽ/ቤታችን ሳንፕል ክፍል ማስገባት ይኖረባቸዋል።
  9.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ኮ/ቀራኒዮ ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301

ስልክ ቁጥር 0118350897

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል

አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration Design & Construction Works Pool Administration Finance Office
  • Bid bond: 15,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 28, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders