በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 14 እና ባለ20፣ የተለያዩ የእርሻ መሳሪያ እና የጥቁር ጥላ መረብ ግዥ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለብሄራዊ አቮካዶ ልማት ፕሮግራም አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 14 እና ባለ20
  • ሎት 02 የተለያዩ የእርሻ መሳሪያ
  • ሎት ዐ3 የጥቁር ጥላ መረብ ግዥ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ተጫራቾች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕለስቲክ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃወች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ለሎት 01 ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና ለሎት 02 100,000.00/አንድ መቶ ሺብር እንዲሁም ለሎት 03 ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( unconditional Bank Guarantee)ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያዉ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።ማንኛውም ተጫራች የጨረታ/የመወዳዳሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሺያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
  8. ቀኑ ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849/ 058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል። ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።
  12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Agriculture Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Apr 28, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders