የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር AAPC NCB 009/2018 ዓ/ም
የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
|
001 |
የፖሊስ ሴፍቲ ጫማ (ቦቲ ጫማ) ግዥ |
በተቋሙ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
200,000 |
00 |
|
002 |
አዲሱ ፊልድ ጃኬት ግዥ |
በተቋሙ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
400,000 |
00 |
|
003 |
1/2 የታሸገ ውሃ ግዥ |
በተቋሙ ፍላጎት |
150,000 |
00 |
|
004 |
የበርላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሎጎና ጽሁፍ ግዥ |
በተቋሙ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
20,000 |
00 |
|
005 |
የተቃጠለ ዘይት በበርሜል የሽያጭ አገልግሎት |
በተቋሙ ፍላጎት |
50,000 |
00 |
|
006 |
ተሽከርካሪ ላይ የተገጠመ ሳይረን የመፍታት የአገልግሎት ግዥ |
በተቋሙ ፍላጎት |
30,000 |
00 |
|
007 |
የካሜራ እና ተያያዥ እቃዎች ግዥ (የፎቶ ካሜራ) |
በተቋሙ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
150,000 |
00 |
|
008 |
የጋወን ጨርቅ (6000) ግዥ |
በተቋሙ ፍላጎት |
10,000 |
00 |
|
009 |
የመፅሄት ህትመት ከነላይ አወትና ዲዛይን ግዥ |
በተቋሙ ፍላጎት |
10,000 |
00 |
ስለዚህ፡-ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፤፤
6. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
7. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን/ፋይናሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው ።
9. ማንኛውንም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትከክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ፣ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
10.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
11. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፣
12. በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት።
13.ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀርቡአቸው ዕቃዎች ተቋሙ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ/sepeciification/መሰረት መሆኑን በተቋሙ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።
14. ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
15. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በተቋሙ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
16. በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፣
17.ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥ 0118 62-58-00 (0111 110 448)
የአ/አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-09
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Police Commission
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.