የጤና መረዳጃ እድር በ240 ካ/ሜ ቦታ ላይ የመጋዘንና ቢሮ ግንባታ ሥራ ለአልሚ ባለሃብት በመስጠት ማስገንባት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ (ግንባታ)
የጤና መረዳጃ እድር በ240 ካ/ሜ ቦታ ላይ የመጋዘንና ቢሮ ግንባታ ሥራ ለአልሚ ባለሃብት በመስጠት ማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህ ሂደት እድሩ መሬቱን የሚያቀርብ ሲሆን አልሚው ባለሃብት በፊናው የግንባታውን ሙሉ ወጪ በመሸፈንና በመገንባት ግንባታውን ለእድሩ ያስረክባል። አልሚው ባለሃብት ያፈሰሰውን ገንዘብ ታሳቢ በማድረግ ለ15 ዓመታት በተመጣጣኝ ዋጋ መጋዘኑና ቢሮውን ተከራይቶ እንዲጠቀምበት ይደረጋል።
በተጨማሪ የአልሚው የግንባታ ወጪ በ15 ዓመታት ውስጥ ከኪራይ ገቢው እየተቀነሰ የሚመለስለት ይሆናል፡፡ ይህም በውልና ማስረጃ ቢሮ በኩል በሚደረግ የውል ስምምነት የፀና ይሆናል።
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማንኛውም ተጫራች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 1000 በመክፈል ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ከ30/8/2018 ዓ.ም 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሰነዱን የመጨረሻ ማስረከቢያ ቀን 10/9/ 2018 ዓ.ም በ6፡00 ይሆናል።
ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ይከፈታል።
እድሩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: የጤና መረዳጃ እድር ቢሮ በኮ/ቀ/ክ/ ከተማ ዓለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሆኖ በወረዳ 4 ቀጠና 1 በተለምዶ ሊዲያ ክሊኒክ ተብሎ በሚጠራው ቅያስ አንድ መቶ ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው ሰፊ አረንጓዴ ሥፍራ ግቢ ውስጥ ይገኛል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911 216 358 / 0911 471 538
የጤና መረዳጃ እድር
Tender details
- Deadline: 2026-05-18
- Publishing entity: የጤና መረዳጃ እድር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.