በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለቶጎ ጫሌ መገንጠያ ጅጅጋ ኤርፖርት የአስፋልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ለአማካሪ ድርጅቱ ሠራተኞች ለፕሮጀክቱ ሥራ እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚውል በቁጥር (4) አራት ዳብልካፕ ተሽከርካሪ መከራየት ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ ኪራይ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለቶጎ ጫሌ መገንጠያ ጅጅጋ ኤርፖርት የአስፋልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ለአማካሪ ድርጅቱ ሠራተኞች ለፕሮጀክቱ ሥራ እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚውል በቁጥር (4) አራት ዳብልካኘ ተሽከርካሪ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም አከራዮች የሚያቀርቡት ዳብል ካፕ ተሸከርካሪ የሥሪት ጊዜው እኤአ ከ2010 ጀምሮ እንዲሁም የፈረስ ጉልበታቸው ከ2800cc ጀምሮ (በላይ) የሆነ ሲሆን ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት፣
3. የባለቤትነት መታወቂያ ሊብሬ የሚያቀርብ፣
4 የ3ኛ ወገን መድን ሽፋን የተገባለት፣
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ ወይም ቢድ ቦንድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በፖስታ አድርጎ በማሸግ ተሽከርካሪው በቀን የሚከራይበትን ዋጋ ግልጽ በሆነ መልኩ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ነዳጅ እንዲሁም የጥገና፣ የሾፊር ደሞዝና አበል በአከራይ ይሸፈናል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322267979 (የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሰራ አምስት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬድዋ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
11. አሸናፊ ተጫራቾች አጠቃላይ የቴክኒክ ምርመራውን ካለፈ ውል በመፈፀም ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት አለባቸው፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር
+0251111313/0929063249 /09-67-47-44-90 /0927636126 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬደዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-05-15
- Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.