የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ለቴ/ከ/ጤ/ጽ/ቤት የእናቶች ማቆያ፣ ቢሮ፣ ስቶር በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ለቴ/ከ/ጤ/ጽ/ ቤት የእናቶች ማቆያ፤ ቢሮ፤ ስቶር በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችዋል።

1ኛ. ተጫራቾች በተሰማሩበት የግንባታ ሥራ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2ኛ. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

3ኛ. ተጫራቾች የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ።

4ኛ. የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

5ኛ. ተጫራቾች የ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ የገቢ ኪሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

6ኛ/ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያቀርቡ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቴፒ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።

7ኛ. ተጫራቾች ህጋዊ ሰውነት ሰርትፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

8ኛ. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታዉ በአሥራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰአት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

9ኛ. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው።

10ኛ. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ቴ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 በመቅረብ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

11ኛ/ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

12ኛ. በጨረታው መከፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ካልተገኙ መስርያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

13ኛ. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የቴፒ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-16
  • Publishing entity: Tepi City Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Apr 29, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders