የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/ግጨ/09/2018 ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች
በጨረታው መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈርም አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ውይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- መገናኛ ስሪ ኤም ሲቲ ሞል ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 639-4655/ 011 639–3010 መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-12 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Transport Bureau
- Buyer address: መገናኛ 3ኤም ሲቲ ሞል 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 30, 2026
- Posted at: 2026-04-30T07:42:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.