የአክሲዮን የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ጀሚላ መሀመድ እና የፍ/ባለዕዳ ያሲን አብዱራህማን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/300535 በ30/03/2017 ዓ.ም እና በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/335434 በ08/04/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በፍርድ ባለዕዳ አቶ ያሲን አብዱራህማን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በአዋሽ ፐብሊክ ኮኔክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ውስጥ የሚገኝ 11,250 (አስራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) የሆኑት አክሲዮን የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) የጠቅላላው የአክሲዮን ዋጋ 11,250,000 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በየካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.335435 በቀን መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛው 2,812,500 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-06-02 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 30, 2026
- Posted at: 2026-04-30T07:55:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.