በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 32/2018
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተርሳይክል እና የተሸከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንዕጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ነዳጅ፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ለውዝ፣ እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀውሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲፒአ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወከሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።
5.ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀሚሮ የምቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፍ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት COP ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 444 1415/ 046 444 1564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Publishing entity: Moyale Customs Branch Office
- Bid bond: በግልፅ ጨረታው 5% እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: May 01, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.