የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የመኪና ጎማና ከመነዳሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

የመኪና ጎማና ከመነዳሪ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ግ/01/2018

የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የመኪና ጎማና ከመነዳሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

.

የዕቃው አይነት

ብዛት

1

የከባድ መኪና ጎማ ከነከመነዳሪው

49

2

የትንሽ መኪና ጎማ ከነከመነዳሪው

50

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በላይ በተገለፀው ዝርዝር መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣

  • የ2018 ዓ.ም የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ( የቫት ) ተመዝጋቢ የሆነ፣

2. የጨረታ ዋስትና መያዣ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ ግዥውን በሚፈፅመው ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል። ከተጠየቀው ውጪ የሚቀርብ ማስረጃ ተቀባይነት

3. የተዘጋጀውን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።

5 ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና 2/ሁለት/ ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከ/መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት በግዥ ቡድን መሪ በመምጣት የተዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ።

8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ግን 21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046-212-1580 ወይም 046-212-9112 ፖ.ሣ.ቁ 108

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልገሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-21
  • Publishing entity: Hawassa City Water and Sewerage Service Organization
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 01, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders