በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ነቀምት እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምግብ እህልና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሸ/03ሠነድ/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ነቀምት እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ
1. ማኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Supply Sector) ስም የጨረታ ማስከበሪ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ አለበት።
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፣
5. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት። ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።
6. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
8. የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።
9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የምግብ ዓይነት የሚሰጠውን ዋጋ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ጽ/ቤት እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል።
10.መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 09 11 31-35-79 አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Ethiopian Seed and Forest Product Supply Sector
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 01, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.