የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የህጻናት ማቆያ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ለቴ/ከ/ሴ/ህ/ወ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት የህጻናት ማቆያ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማሰራት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችዋል።

1ኛ. ተጫራቾች በተሰማሩበት የግንባታ ስራ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2ኛ. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት የምስከር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

3ኛ. ተጫራቾች የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡

4ኛ. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

5ኛ. ተጫራቾች የ2017 በጀት አመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ የገቢ ኪሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

6ኛ/ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያቀርቡ ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቴፒ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።

7ኛ. ተጫራቾች ህጋዊ ሰውነት ሰርትፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

8ኛ/ ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰአት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

9ኛ. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10ኛ/ ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ቴ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 በመቅረብ ብር 500 (አምሰት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

11ኛ/ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ ለጨረታ ውል ማስከበርያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

12ኛ በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ መስርያ ቤቱ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

13ኛ. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-18
  • Publishing entity: Tepi City Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ)
  • Published: May 01, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders