በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ነቀምት እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምግብ እህልና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሽ/03ሠነድ/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ሀዋሳ፣ ቦንጋ፣ ነቀምት እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Supply Sector ስም የጨረታ ማስከበሪ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፣
- ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት። ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የምግብ ዓይነት የሚሰጠውን ዋጋ በኢንቬሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ጽ/ቤት እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኙ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 09 11 31-35-79 አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 02, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.