በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቂሊንጦ ለሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቂሊንጦ ለሥራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎች አሸዋ፣ የአርማታ ጠጠር፣ የግንባታ ድንጋይ፣ የሃርኮር ድንጋይ፣ የዝግባ ጣውላ የአርማታ ብረት ባለ 10፣ እስታፍ ባለ 6፣ ብሎኬት ባለ 15፣ ላሜንትድ ሚድፋ ባለ 188 ቲክነስ 2240/1220 ሚሚ፣ ቆርቆሮ ባለ 28 ጌጀ፣ አጠና ወራጅ ባለ 12 ሚሚ፣ አጠና ማገር ባለ 6 ሚሚ፣ ኮሚርስቶ ባለ (3 ሚሚ 244/220 ሚሚ፣ ሞራሌ 50 ሚሚ /70 ሚሚ/ባለ 4 ሜትር ቁመት፣ ሞራሌ 40 ሚሚ/50 ሚሚ፣ ኤሊ ቲ ዜድ ብረት፣ የበር ሰረገላ ቁልፊ ፣ቶሪኖ ማጠፊያ መካከለኛ፣ አንተሬስት፣ የፕላስቲክ ቀለም፣ ሲሚንቶ፣ የግንብ አሸዋ፣ 02 ጠጠር፣ ገረጋንት፣ እርዳሽ፣ ተለጣፊ _ ማብሪያ ማጥፊያ፣ ተለጣፊ ሶኬት ሆልደር ባለ 36 ዋት ፊሎረሰንት አምፖል ባለ 18 ዋት፣ ሆለደር ባለ 18 ዋት እስታርተር ኤስ 10፣ ብሬከር ባለ 25 አምፔር፣ የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 4፣ የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 2.5፣ ኮኔክተር 150 አምፔር፣ ፓውዛ ባለ 200 ዋት፣ ሬዚስታንስ ባለ 09 እና 08፣ ናስትሮ፣ የሸክላ ባለ 58 ስፋት፣ ቦዲ ባለ 58 ስፋት፣ የተለያዩ የቧንባ እቃዎች፣ እና ብዛት ያላቸው የጥገና አግልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ማዕከል የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት። ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።

8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ማዕከል የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል።

11. ጨረታው ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

14. መስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ጨረታው በሚከፍተበት ቀን ዝግ የዓመት በዓል ከሆነ በሚቀጠለው ቀን ይከፍታል።

አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ፡- 011 471 6333 / 011 888 6089 / 011 434 8986 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቀ/ማረ/ቤት አስተዳደር/

ቂሊንጦ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-15
  • Publishing entity: Federal Prisons Administration Facility House Administration
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 02, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders