አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የውሃ ማቆሪያ Geomembrane Sheet ምርት በብሔራዊ ግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ምርቱን ለሚፈልጉ ደንበኞች መሸጥ ይፈልጋል

Description

የውሃ ማቆሪያ (Geomembrane Sheet) ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ APF/21/2018/Local

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶችን በብዛት እና በጥራት እያመረተ ለገበያ የሚያቀርብ ፋብሪካ ሲሆን ከሚያመርታቸው የምርት አይነቶች ውስጥ መልኩ ጥቁር Dark Black) የሆነ የውሃ ማቆሪያ (Geomembrane Sheet) አንዱ ነው። ፋብሪካው ይህን በጥራት የሚያመርተውን የውሃ ማቆሪያ Geomembrane Sheet ምርት በብሔራዊ ግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ምርቱን ለሚፈልጉ ደንበኞች መሸጥ ይፈልጋል።

ለሽያጭ የቀረበው የውማ ማቆሪያ (Geomembrane Sheet) ወፍረቱ በአማካይ 0.5 ሚሜ ሲሆን ደንበኞች በሚፈልጉት መሰረት ያልተበየደ (ዝርግ የሆነ) ወይም ፋብሪካው በራሱ ወጪ በጥራት መበየድ ማቅረብ ይችላል።

ያልተበየደው የውሃ ማቆሪያ (Geomembrane Sheet} ርዝመት 28ሜ ወርድ 6.25 ሜ ስፋቱ 175 ካሬ ሜትር ሲሆን የአንድ ካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ ዋጋው ከነቫቱ ብር 206.68 ነው። እንዲሁም የተበየደ የውሃ ማቆሪያ (Geomembrane Sheet) ርዝመት 14ሜ ወርድ 12.5ሜ ስፋቱ 175.36 ካሬ ሜትር ሲሆን የአንድ ካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ ዋጋ ከነቫቱ ብር 207.00 ነው።

ለሽያጭ የቀረበው ምርት ጠቅላላ ብዛት 433,901.64 ካሬ ሜትር ሲሆን ከዚህ ውስጥ

ሎት 1 ያልተበየደው ብዛት 311,325 ካሬ ሜትር

ሎት 2 የተበየደው ደግሞ ብዛት 122,576.64 ካሬ ሜትር ነው።

ስለሆነም ተጫራቾች ከግንቦት 01 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለጨረታ የቀረበውን ምርት አጠናቀው የማንሳት ግዴታ አለባቸው። በመሆኑም ከዚህ ቢታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ (መወዳደር) ይችላሉ።

1. ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ተያያዥ የሆኑ የሕጋዊነት ሠነዶችን ማለትም የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት (Certificate) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ቅጅ (Copy) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የተወዳደሩበትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Irrevocable & Unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም " Amhara Pipe factory Plc" በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።

3. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 ማግኘት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሠነዶቻቸውን ቅጅ (Copy) የመወዳደሪያ ዋጋቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

5. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8:00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። በጨረታው መከፈቻ ዕለት የሚገኙት የተጫራች ድርጅቶች ተወካይ ወይም ባለቤት ህጋዊ የፍትሕ ውክልና ወይም የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሠራተኛ ስለመሆኑ ከድርጀቱ የተፃፈ ደብዳቤ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

6, 10ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

7. የውድድሩ አሸናፊ የሚለየው በየሎቱ ሲሆን በሎቱ ለተጠቀሰው ምርት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል።

8. አሸናፊው አሸናፊዎች ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ በኩል ማረጋገጫ የተሰጠበት የባንክ ዋስትና (Irrevocable & Unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም "Amhara Pipe Factory Pl' በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት እለት ጀምሮ ባሉት በ3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለበት።

9. የውድድሩ አሸናፊ ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ አሸናፊ የሆነበትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ 50% ውል በተያዘ በ3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት።

10. ፋብሪካው ማንኛውንም ዓይነት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን ምርቶች በአካል በፋብሪካው አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 09 35 98-37-29/ 09 18 70-18 26/ 09 00 90 92 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-05-14 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
  • Buyer TIN: 0006196550
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 03, 2026
  • Posted at: 2026-05-04T08:04:31.000Z
  • Buyer website: https://amharapipe.et/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders