ሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የተሰማራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- Disposal 001/2018

ሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የተሰማራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

1. በጨረታ የሚሳተፍ ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች ሀዋሳ ፒያሳ ሀዋሳ ሀይቅ የገበያ ማዕከል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ስም በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013518088 በማስገባት ያስገቡበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለጨረታ ያቀረቡትን 10% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የሚፈልጓቸውን የተሽከርካሪ አይነትና የሰሌዳ ቁጥር ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ከሲ.ፒ.ኦ. ጋር በማካተት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 13ኛ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡30 ሀዋሳ ፒያሳ ሀዋሳ ሀይቅ የገበያ ማዕከል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ለመረጡት ተሽከርካሪ ፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ። ጨረታው በእለቱ 4፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ሀዋሳ ፒያሳ ሀዋሳ ሀይቅ የገበያ ማዕከል አጠገብ በሚገኘው ፓርኪንግ ላይ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስራ ሶስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ተሽከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ።

6. የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዟቸው ተሽከርካሪዎች የስም ማዘዋወሪያ ወጪ በራሳቸው ይሸፍናሉ።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ/ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሸከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን ማንሳት ሲኖርበት ተሽከርካሪውን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው CPO እንዲወረስ ይደረጋል።

8. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች በ 3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ እንዲመለስ ይደረጋል።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብት አለው።

አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ ሀዋሳ ሀይቅ የገበያ ማዕከል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410

ማሳሰቢያ፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 24 09 80/ 09 30 06 94 87 ይጠቀሙ። ተጫራቾች ሙሉ አድራሻና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።

ሪሰረክሽን ኤንድ ላይ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-16
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 13ኛ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-16 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 13ኛ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Resurrection and Life Development Organization
  • Buyer address: ሀዋሳ ከተማ ወደ አዲስ አበባ መውጫ ከሊፋን የመኪና ታፔላ ፊት ለፊት ወደቀኝ ገባ ብሎ በ50 ሜትር ላይ ነው
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 03, 2026
  • Posted at: 2026-05-04T08:07:48.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders