በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ያሉ ግንባታና አቅርቦቶች በብሔራዊ ገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት እና መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጨ-1/3057/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ከተራ ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 2 ድረስ ያሉ ግንባታ ና አቅርቦቶች በብሔራዊ ገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት እና መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

1. ባለ 4 ወለል ህንጻ ግንባታ ህንፃ ተቋራጭ /BC/ ከሆነ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላል በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ/GC/ ከሆነ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላል።

2. የህንጻ መሳሪያ

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል

1. ተጫራቾች በዘርፋ የ2018 ዓ/ም ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የግዥ መጠናቸው ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር /እና በላይ ከሆነ የተጨማረ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. በፌ.ዴ.ራ.ል ደረጃ ካላቸው የምስክር ወረቀት በተጨማሪ በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የአጭር ግዜ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. የግንባታውም ሆነ የአቅርቦቱ አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ

7. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ለህንፃ ግንባታ በአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በተራ ቀጥር 2 ለተገለጸው የህንጻ መሳረያ ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር /በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘዉትር በስራ ስዓት ከገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።

8. የግንባታው ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ /ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። የእቃ ግዥ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት /ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደረበት የግንባታም ሆነ አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፋያ ትእዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታሳይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሰቆጣ ወረዳ ገ/ኢ/ጽ/ቤት በመ/ሂ-1 ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

10. ማንኛውም ተጫራቾች የህንጻ ግንባታ ስራ ፋይናሻሱን እና ቴክኒካል መረጃዎችን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የእቃ ግዥ ከ 25/08/2018 እስከ 09/9/2018 ዓ.ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፣ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 10/09 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጉ በ4፡00 ሰዓት ግዥ /ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል። ግንባታ ስራን ከ 25/08/2018 እስከ 15/9/18 ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን። በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው፣ ፌርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 16/9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ታሸጉ በ4፡00 ሰዓት ግዥ /ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል።

11. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገm/CPO / ወይም በጥሬ ገንዘብ /መሂ-1 በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው።

12. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበረያውን የመውረስ መብት አለው።

13. መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ለቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ሕጋዊ ተወዳዳሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ አይነትና የግዥ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ መሰረት የመሙላት ግዴታ አለበት።

14. አሸናፊው የአሸነፈውን ግንባታ ከሚፈለግበት ቦታ ሰርቶ የማስረከብና ገዥውን በሚፈለግበት ሴክተር መ/ቤቶ በማስረከብ ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግዴታ አለበት።

15. በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቅረብ አለባቸው። ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።

16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 0416 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

17. መ/ቤቱ የተሸለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

18. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

19. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ሳይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት CENTRAL GONDAR ZONE HIGH COURT

በዋግ ኽምራ መስተዳደር ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የሰቆጣ ወረዳ ገንዘብና ፕላን ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-24
  • Publishing entity: Sekota Woreda FEDB
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: May 03, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders