በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘርፉ የ2018 ታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በቁ 1 - 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ(ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፎቶ አብሮ የተያያዘ ሲሆን በአካልም ቢሮ ቁጥር 108 በመምጣት ማየት ይቻላል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 101 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ/ዳይሮክቶሪት ቢሮ ቁጥር 107 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት ከጥዋቱ 3፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 3፡05 ሳጥኑ ይታሸጋል
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል። ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ጨረታው የሚገመገመው በሚቀርበዉ የተናጠል ዋጋ ነዉ
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 107 ድረስ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባህል
ቱሪዝምና እና ስፖርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-20
- Publishing entity: አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባህል ቱሪዝምና እና ስፖርት ቢሮ
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 05, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.