በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም የስፖርት ትጥቆች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የስፖርት ትጥቅ የወጣ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 03/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም የስፖርት ትጥቆች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸውን የሚገልፅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች በሚወዳደርበት ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ (የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፤ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፤ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለፅ አለበት።

4. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ፋ/ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቭሎፕ አርጅናል እና ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቶች ማዕከሉ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የግብዓቶችን ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲ.ፒ.ኦ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት በ10ኛው የሥራ ቀን 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልፅ ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው (ጨረታ በሚከፈትበት) ቀን 4፡30 እስከ 5፡30 ባለው ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በተባለው ሰዓት ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል።

12. ተጫራቶች ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸንፉበትን ግበአት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል ፡፡ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገልፃል።

13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዕከሉ ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

14. ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተ ግራ ገባ ብሎ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Publishing entity: Ras Hailu Sport Education and Training Center
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 04, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders