በደ/ምዕ ኢ/ሕ/ክ/መ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም በጀት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የተለያዩ ግንባታዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ ኢ/ሕ/ክ/መ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም በጀት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ

  • በሎት 1 የጨልሾ የእንስሳት ጤና ኬላ አንድ ብሎክ ሕንፃ ግንባታ፣ አንድ የእንስሳት ማዳቀያ ግንባታ እና ዙሪያ አጥር ሥራ
  • በሎት 2 የካውካ እንስሳት ጤና ኬላ አንድ ብሎክ ሕንፃ ግንባታ አንድ የእንስሳት ማዳቀያ ግንባታ እና ዙሪያ አጥር ሥራ
  • በሎት 3 የማይላ የሰው ጤና ኬላ ግንባታ
  • በሎት 4 የሰሙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ውስጥ
    • 1ኛ አንድ ነባር የምንጭ አይን ግንባታ
    • 2ኛ አንድ አዲስ 25 ሜትር ኩብ ማጠራቀሚያ ግንባታ
    • 3ኛ አንድ አዲስ ቦኖ ግንባታ ሥራ
    • 5 ሁለት ነባር የሕዝብ ቦኖ ጥገና ሥራዎች
    • 5ኛ አንድ የልብስ ማጠቢያ ገንዳ ጥገና ሥራ
    • 6ኛ አንድ የእንስሳት ውሃ ማጠጫ ገንዳ ግንባታ ሥራ
    • 7ኛ የውሃ ቱቦ መስመር ዝርጋታ ሥራ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

1/በዘርፉ ለ2018 ዓ.ም የታደስ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው

2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3/ በመንግሥት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ያለው

4/የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TN no) ያለው

5/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት

6/ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም ለሎት 4 ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል ከውሃ ማዕድንና ኢነርጅ ሚኒስቴር የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችልና ደረጃውን በተመለከተ 5 (አምስት) እና ከዛ በላይ GC/BC እና ለሎት 4 GC ወይም የውሃ ሥራ ተቋራጭነት ፍቃድ ያለው መሆን አለበት።

7/ ከማንኛውም ታከስ ዕዳ ነፃ ስለመሆኑ ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።

8/ ከዚህ በፊት ያለውን የድርጅቱ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከተለያየ ድርጅቶች የተሰጠ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ወዲህ ያለዉን ማቅረብ የሚችል።

9/ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) CPO/ የባንክ ጋራንቲ/ጥሬ ገንዘብ ከታወቀ ባንክ በአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ስም በማዘጋጀት በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10/ ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በአካውንት ቁጥር 1000521691305 በማስገባት የባንክ አድቫይስ ይዞ በመምጣት በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

11/ አንድ ተጫራች ከሁለት በላይ ሎት መወዳደር አይችልም እንዲሁም ከሁለት በላይ ሰነድ መግዛትም አይችልም።

12/ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ የደ/ም/ኢት/ሕ/ክ/መንግሥት አደጋ ስት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ዶክመንቶች በመግዛትና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት እያንዳንዱን ሎት ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በአንድ እናት የጨረታ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የደም ኢት/ሕ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

13/ ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዶክመንት ላይ በመፈረም ማህተም በማድረግ በፖስታ ጀርባው ላይ በሚታይ ጽሑፍ ሎቶቹን ለይቶ መጻፍ አለበት።

14/ የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ም/ኢት/ሕ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶረት ቢሮ ይከፈታል።

15/ በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች የመወዳደሪያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል።

16/ የሂሳብ ስህተት ከጠቅላላ ድምር ከፍታ እና ዝቅታ 5% በመመሪያው መሠረት ተግባራዊ ይሆናል።

17/ በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ተጫራች ብቻ ወደ ድህረ ግምገማ ያልፋል።

18/ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቦታው ላይ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈትን አያስተጓጉልም።

19/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 0920 925 053

አድራሻችን፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ውስጥ የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ቢሮ ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 145 ኪ.ሜ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በስተምዕራብ 165 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በታርጫ ከተማ ይገኛል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-26
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-26 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South West Ethiopia Peoples Regional State Fire and Disaster Management Commission
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: May 05, 2026
  • Posted at: 2026-05-06T12:54:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders