Livestock and breeding stock
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የእንሰሳት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ አርሶ አደር ቤተሰቦች በድጋፍ መልክ የሚሰጡ የእርባታ በጎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ማህበራት፣ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የእርባታ በጎች ግዥ ጨረታ
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የእንሰሳት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ አርሶ አደር ቤተሰቦች በድጋፍ መልክ የሚሰጡ የእርባታ በጎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ማህበራት፣ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፎቹ የተሠማራችሁና በጨረታዉ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸሁ፣
- በእንሰሳት አቅራቢነት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ማህበራት፣ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች
ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 07 (ሰባት) ቀናት የጨረታ ሠነዱን በብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ቀይት ከሚገኙ የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ከባንክ ሲፒኦ ጋር በፖስታ አሽጎ በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን ጨረታዉ በ8 ኛዉ ቀን በ5፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ5፡30 ሠዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን 8ኛዉ ቀን በካላንደር የሚዘጋ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳዉቃለን።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
ደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀይት ቀበሌ
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-656-0249 ወይም
ኢሜል፡ [email protected]
Tender details
- Deadline: 2026-05-14
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛዉ ቀን በ5፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-05-14 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛዉ ቀን በ5፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tesfa Berhan Child and Family Development Association
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (May 06, 2026)
- Posted at: 2026-05-06T13:05:40.000Z