ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ አሸዋና ድንጋይ እንዲሁም ለተማሪዎች ቀለብ የሚውል ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 32/2018 ዓ/ም
ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ አሸዋና ድንጋይ እንዲሁም ለተማሪዎች ቀለብ የሚውል ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ ይችላሉ።
- አድራሻ በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ነዉ።
- በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕረይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 001 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ። የሚገዛዉ ዕቃ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሆነው ለሚገዛው እቃ በQR COD በታተመ ደረሰኝ የሚስጥ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉባቸዉን ውል መያዝ አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆ። ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ። ሰነዱን የወሰዱት ሁሉም ተጫራቾች ከመክፈቻ ቀን በፊት ሁሉም ከመለሱልን የመክፈቻ ቀን ሳንጠብቅ የምንከፍት ይሆናል።
- አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 (ሰባት) ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ።
- ኢተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር 3 በመቶ እና 15 በመቶ ቫት እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙላት አለባቸው።
- ኢንተርፕራይዙ ባወጣው ጨረታ ላይ 50 በመቶ የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች
ኢተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-05-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-14 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Sutana Trading and Consultancy Enterprise
- Published: May 04, 2026
- Posted at: 2026-05-07T06:35:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.