የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ጤፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለእህል ሸያጭ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ነጭ ጤፍ 2774 ( +) ኩንታል ሠርገኛ ጤፍ 1,350 ( +) ኩንታል ቀይ ጤፍ 517 ( +) በጠቅላላዉ 4,596 ( +) ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾቹ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ ገበያ መምሪያ በብር 1000.00 መግዛት ይችላሉ።

2. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤፤

3. ተጫራቾቹ እህሎቹ ያሉበትን ሁኔታ አምቦ ከተማ በሚገኘው የዩኒዬኑ መጋዘን በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስላቸው ይሆናል።

5. ጨረታው ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል። 21ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፤

6. ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ በሰዓቱ ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠያቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ ጨረታውን በእንዱ የእህል ዓይነት ወይም በሁሉም የእህል ዓይነት ላይ መጫረት ይችላል።

9. ጨረታውን ያሸነፈ አሸናፊ ለውል ማስከባሪያ የጠቅላላውን ግዥ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ላይ 5% ለዋስትና በባንክ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

10. ዩኒየኑ ለእህሉ ሽያጭ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0112 609 101 ወይም 0112 363 399 ይጠቀሙ፣

አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-27 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ambo Farmer's Cooperative Union
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published: May 07, 2026
  • Posted at: 2026-05-07T12:33:50.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders