በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን የፕላስትክ ፋብሪካ የቀጣይነት (REVITALIZATION OF PP BAG FACTORY) ጥናት እና የማማከር አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን የፕላስትክ ፋብሪካ የቀጣይነት (REVITALIZATION OF PP BAG FACTORY) ጥናት እና የማማከር አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ይህንን ጥናት እና ማማከር ሥራ መስራት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፡-
1. ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያለው እና የዓመቱን ግብር የከፈለ
2. ለጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በዩኒየኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087184327 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000036818348 በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየን መውሰድ አለባቸው።
3, ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ ያቀረቡትን ዋጋ 5% በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ሰነድ ማስያዝ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ 17/09/2018 ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒየኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ኣለባቸው።
5. የጨረታ መክፈቻ ቀን በ17/09/2018 ሳጥኑ ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
7. ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ሥራ በ10 ቀን ውስጥ መጀመር ይኖርበታል።
አድራሻ፡- በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80 ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 09 11 08 00 03 / 09 12 12 29 71 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የበቾ ወሊሶ የገበሬዎች የሕብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-25 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Becho-Woliso Farmers Cooperative Union
- Buyer address: በጅማ መንገድ ከአ/አበባ 80 ኪ.ሜ ርቀት ቱሉቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 08, 2026
- Posted at: 2026-05-08T07:32:26.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.