በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎ/ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች አወዳድሮ በሽያጭ ማስወገድ እና አዳራሽ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎ/ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 1. የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ሎት 2. የውጭ ፈርኒቸር ሎት 3. የጽዳት እቃ ሉት 4, ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ሎት 5. ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የስፖርት ትጥቅ ሎት 6 ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት /ለማስገንባት/ ይፈልጋል እንዲሁም ሎት.7 የተለያዩ የአገለገሉ እቃዎች አወዳድሮ በሽያጭ ማስወገድ ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

በዚህም፡-

1. በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያደሱ ሲሆን ።

በሎት.7 የተጠቀሰውን በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የግዥው መጠን ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። በሎት 7 የተጠቀሰውን ከቁጥር 1-3 የተገለጹትን ማስረጃዎችን ተወዳዳሪዎች እንዲያቀርቡ አይገደዱም።

4. የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ላይ የሚሳተፍ በዘርፉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ከከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራገክሽን ማቅረብ የሚችል እና በፌደራል ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ተቋራጭ በክልሉ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን የአጭር ጌዜ ምዝገባ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ምዝገባ ማድረግ ይኖርበታል።

5. የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ የተቋራጭ ደረጃ BC/GC 6 እና ከዚህ በላይ የሆነ

6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት በሎት 7 የተጠቀሰውን ከቁጥር1-5 የተገለጹትን ማስረጃዎችን ተወዳዳሪዎች እንዲያቀርቡ አይገደዱም።

7. በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለእቃና አገልግሎት ለ40 ቀን ፀንቶ የሚቆይ እና ለመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ለ60 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፣

8. የሚገዙ እቃዎችን/አገልግሎቶች/ እና የተለያዩ የአገለገሉ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በምስ/ጎጃ/ዞን ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን ለገንዘብ ያዥ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 01 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት 1. የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች 20,000/ሃያ ሺህ/ ብር ሎት 2. የውጭ ፈርኒቸር 10,000/አስር ሺህ/ ብር ሎት 3.የጽዳት እቃ 10,000 /አስር ሺህ ብር ሎት 4 ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የኤሌክትሪክ እቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ብር ሎት 5. ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የስፖርት ትጥቅ /5,000/አምስት ሺህ/ብር ሎት 6. የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ሎት 7. የተለያዩ የአገለገሉ እቃዎች በሽያጭ ማስወገድ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በመ/ቤቱ መሂ-1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና / ቢድ ቦንድ/ ማስያዝ አለባቸው።

11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእቃና አገልግሎት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ግን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉና ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ የመወዳደሪያ ሃሳብ ሞልቶ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጨረታው በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን እና ለግንባታው በተመሳሳይ ሰዓት 31ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መምሪያው ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን እንዲታወቅ፤ ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓላት ቀን ወይም የካላንደር ዝግ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

12. የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ስርዝ ድልዝ ከሆነም ፓራፍ መደረግ አለበት፤ ኮሬክሽን ፍሉድ መጠቀም ወይም መፋቅ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ሎት 6 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ላይ የተጠቀሰው ስርዝ ድልዝ ወይም ኮሬከሽን ፍሉድ መጠቀም ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።

13. ተጫራቾች መ/ቤቱ ካዘጋጀው የስራ ዝርዝር /ስፔስፍኬሽን/ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።

14. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ ሲሆን ሙሉ በሙሉ የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡ የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ዋጋ ሙሉ በሙሉ _ አለመሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡ ሆኖም በሎት 7 የተጠቀሰውን ግን አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ሲሆን ጨረታው አሸናፊ የሚለየው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።

15. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ወይም ውል የያዙባቸውን እቃዎች በምስ/ጎ/ዞን መምሪያዎች ባሉ የፑል ንብረት ከፍሎች ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም በሎት 7 የተጠቀሰውን ግን ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ10 ቀናት ውስጥ እቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል።

16. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

17. ተጫራቾች በመ/ቤቱ ለአንድ ያገለገሉ እቃዎች ወይም የዋጋ አይነት ከተገለጸው መጠን ብዛት ውስጥ ቀንሰው መወዳደር አይችሉም

18. ለሽያጭ የቀረበው ያገለገሉ እቃዎች መነሻ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጿል

19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

20. በጨረታ ማስታወቂያዉ ያልተሸፈነዉን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ በተመለከተ በ2014 ዓ/ም ከገንዘብ ቢሮ በተላለፈው የግንባታ መመሪያ መሰረት የሚታይ ይሆናል።

21. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምስ/ጎጃ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 6817 በመደወል ማግኘት/መጠየቅ ይችላሉ።

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎጃ/ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-08 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ ጎ/ዞ/ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: May 09, 2026
  • Posted at: 2026-05-09T08:15:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders