የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት የአትክልት ዘር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EB/ MAS/024/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት የአትክልት ዘር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ተጋብዘዋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ እነዚህን ሰነዶች አሟልቶ ያልቀረበ ተጫራች በውድድሩ ሊሳተፍ አይችልም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 15 ማግኘት ይችላሉ
6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአትክልት ዘር ብር 300,000 /ሦስት መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በቢሮው ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ እስከ ጧቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብስባ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 1666/058 320 5654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-25 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4:30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara National Region Authority Education Bureau
- Bid bond: 300,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: May 10, 2026
- Posted at: 2026-05-11T10:43:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.