በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም፦
የሲኖ ትራክ (SINO Truck) የኒሳን ዮዲ(Nissan UD)፣ የኪያ (KIA)፣ የፉቶን ዳምፕ ትራክ (Foton Dump Truck)፣ ፎርክሊፈት(Forclift) የሎደር (Loader) የኤክስካቫተር (Exavator)፣ የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) የዳምፐር (Damper) ፣ የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ(ZNA pick up) ፣ ሪች (Rich) ፣ የቢሾፍቱ ፒክ አፕ(Bishoftu pick up)፣ የፎቶን ፒክ አፕ(Foto pick up) የፎርላንድ (Forland)፤የፋዎ ቤላ(FAW BELLA)፤ የኦቲንግ(Oting)፤ የፎቶን ሚኒ ባስ (Foton mini Bus)፣ ሙዳን ባስ(Mudan Bus) ኤፍሲአር(FSB)፣ ጋርቤጅ ቲፐር(Garbage Tipper)፡ ካኒባላይዝ (Canibalize) ኪያ (KIA) እና ዎኪንግ ትራክተር (Walking Tractor) መለዋወጫዎችን(Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ።
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 ሶስት መቶ ብር በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይመስቀል ወስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ትቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ካዲስኮ ዋና መስራቤት የበላይአብ ሞተርስ ግቢ ዉስጥ መውሰድ ይችላሉ።
አድራሻ
በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሞባይል ፡- 0966 21 51 83/84
ስልክ ፡- 0114 343691
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-22 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Belayab Motors P.L.C.
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 10, 2026
- Posted at: 2026-05-11T14:06:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.