በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የባዶ ኮንቴነር ማመላለሻ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ESLSE/P&T/REQ/2025/02712
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለኤክስፖርት የሚያገለግሉ ባዶ ኮንቴነሮችን ለማስጫን ስለፈለገ የሀገር ውስጥ የጭነት ትራንስፖርት አክሲዎን ማህበራትን በማወዳደር ካሸናፊው ማህበር ጋር ውል በማሰር ማሠራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተቀመጡትንመስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ሎት-አስር፡ የባዶ ኮንቴነር ማመላለሻ አገልግሎት ግዥ
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስክር ወረቀት የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠ ማስረጃ (Valid tax clearance)፤
- የታደሰ ሶስተኛ ወገን እና ኢንሹራንስ ሰነድ ማቅረብ የሚችል።
- ከትራንስፖርት ባለሥልጣን የተሰጠ የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ከነ ሰሌዳ ቁጥር ወይንም የተሽከርካሪዎችን የባለቤትነት ደብተር (ሊብሬ) ዝርዝር ማቅረብ የሚችል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በንግድ ባንክ፣ በህብረት ባንክ ወይንም በኦሮሚያ ህ/ሥራ ባንክ ብቻ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድረ-ገጽ (WWW.ESLSE.COM)ላይ በERP SYSTEM በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ሰዓት ይሆናል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 022 116 2194 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ
የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-06-12
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ሰዓት ይሆናል
- Bid opening: 2026-06-12 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ሰዓት ይሆናል
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Shipping and Logistics Services Enterprise
- Buyer address: ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው የጉምሩክ ግቢ/ የቀላል ባቡር ግቢ አጠገብ የድሮ ኮሜት ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Published: May 13, 2026
- Posted at: 2026-05-13T08:25:20.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.