የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ የመኪና ሞተር ዘይት እና ቅባት፣ የመኪና ጎማ፣ የፋብሪካ ማቴሪያል፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪና እቃ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሎት 1 የመኪና ሞተር ዘይት እና ቅባት፣ ሎት 2 የመኪና ጎማ፣ ሎት 3 የፋብሪካ ማቴሪያል፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 5 የመኪና እቃ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ አካላት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መወዳደር ይችላሉ።
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው የግዥ መጠን 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ተያይዞ መታሸግ አለበት፣
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ።
አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣
ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎቹ አይነት በሎት በጠቅላላ ድምር ዋጋ ነው።
0. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
1. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል።
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 610 ድሪስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 8118/19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
3. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው አካል ያሸነፈውን ንብረት ደቡብ ወሎ ዞን በሁሉም ንበረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- የመኪና እቃ፣ የዘይትና ጎማ ጨረታ ሰነድ ሲገዙ የተቀመጠውን የመኪና እቃ የዘይትና የጎማ ሳምፕል አይተው ዋጋ ይሙሉ።
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-28 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: South Wollo Zone Finance Command
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 13, 2026
- Posted at: 2026-05-13T08:37:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.