ፀደይ ባንክ አ.ማ Office Furniture እና ለዋና መ/ቤት ህንፃ የዲጅታል ማስታወቂያ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0014/2018
ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር በሰንጠረዥ የተገለፁትን Office Furniture እንዲሁም ለዋና መ/ቤት ህንፃ የዲጅታል ማስታወቂያ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1-Office Furniture
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
ብዛት |
|
1 |
Office/Medium Back Swivel Arm Chair |
200 |
|
2 |
Fixed Gust Chair with arm rest |
300 |
|
3 |
Managerial Table with Drawer 180*90*75 |
49 |
|
4 |
Managerial /High Back Swivel Arm Chair |
49 |
|
5 |
Clerical Table 120*60*75 |
100 |
|
6 |
Three-Seater Guest Chair |
70 |
|
7 |
Notice Board |
100 |
|
8 |
Group Table |
6 |
ሎት-2 - ለዋና መቤት ህንፃ የዲጅታል ማስታወቂያ ለማሰራት
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅትነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ በጨረታ ለመካፈል ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ሊኖራቸዉ ይገባል።
- ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ የ90ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ከም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከስዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታዉ መዝጊያ ስዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 558 1658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-29 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 13, 2026
- Posted at: 2026-05-13T08:46:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.