ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ሆለታ ከተማ አቅራቢያ ለሚገኘው ሲሚንቶ ፋብሪካው በግብዐትነት የሚውል ጥሬ እቃ ወይንም ፑሚስ ለማቅረብ የሚችሉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
Raw material (Pumice) Supply Service/2026
በድጋሚ የወጣ የሲሚንቶ ግብአት (ፑሚስ) አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ
CSC/RM/NCB/002/2018
ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ሆለታ ከተማ አቅራቢያ ለሚገኘው ሲሚንቶ ፋብሪካው በግብዐትነት የሚውል ጥሬ እቃ ወይንም ፑሚስ ለማቅረብ የሚችሉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች አንድ ቶን ፑሚስ ለማቅረብ የሚሰጡትን ዋጋ በፖስታ አሽገው ለግዢ እና አቅርቦት ክፍል እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ከላይ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ፑሚስ ቴክኒካዊ ግምገማ የሚደረግበት መሆኑ እንደተተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉትን ቴክኒካዊ መመዘኛ ሊያሟላ ይገባዋል።
|
የጥራት መለኪያ መስፈርት |
በፑሚስ ውስጥ ሊኖር የሚገባው መጠን |
|
SiO2+Al2O3+Fe2O3 |
>70 |
|
Reactive Silica |
>25 |
|
Moisture (እርጥበት) |
≤15 |
2. ተጫራቾች ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የፈቃዳቸውን ኮፒ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆቸው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የVAT ተመዝጋቢ መሆን የሚገባቸው እና የራሳቸው ጥሬ ዕቃ ማውጫ ቦታ (Quary) ሊኖራቸው ይገባል።
4. ተጫራቾች ለአንድ ቶን የፑሚስ ግብአት ለማቅረብ የሚሰጡትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በሚከተለው መልኩ ዋጋቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የግብዐቱ ዓይነት |
መለኪያ |
የአንዱ ዋጋ (የተ.ዕታን ሳይጨምር) |
|
1 |
ፑሚስ (ማጓጓዣን ሳያካትት) |
ቶን |
|
|
2 |
ፑሚስ (ማጓጓዣን ጨምሮ) |
ቶን |
|
5. አሸናፊዊው ተጫራች ውጤቱ በተገለጸለት ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጥሬ እቃውን ናሙና ለቴክኒካው ምረመራ የማቅረብ ግዴታ የሚኖርበት ሲሆን በተጨማሪም ድርጅቱ የሳይት ጉብኝት በማድረግ በግምገማው ውጤት መሠረት የአቅርቦት ውል የሚፈጸም ይሆናል።
6 ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛው ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ ጌታ አስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ 011 416 3273/ 09 44 12 23 11
ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-20 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Habesha Cement Share Company
- Buyer address: አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ ጌት-አስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
- Published: May 13, 2026
- Posted at: 2026-05-13T09:24:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.