አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የቢ+2 ጂ+4 ህንፃ የግድግዳ ክፍል አልሙኒየም ልባስ ስራ እና ሌሎች የተለያዩ ስራዎች በፋይነት ማሰራት ይፈልጋል

Description

የአልሙኒየም ልባስ

ስራ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ ማህበራዊ ተጠቃሚነት አስተዎጾኦ በማድረግ ተልእኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው። በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኘውን የቢ+2 ጂ+4 ህንፃ የግድግዳ ክፍል አልሙኒየም ልባስ ስራ እና ሌሎች የተስያዩ ስራዎች በፋይነት ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No ያላቸው
  2. የግዥ መጠን 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. በመንግስት ግዥ በአዲሱ አቅራቢዎች ዝርዝር መረጃ ላይ ማለት (https://wwweqp.ppa.gov.et) መመዝገባቸውን የሚችሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመስከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል አዲስ አበባ በሚገኘው አልማ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፤
  7. የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዶክመንት ላይ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፤
  9. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አዲስ አበባ አስማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 መግዛት የሚቻል ሲሆን፤ የጨረታው ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የፋይናንስ ስብቻ የቴክኒክ ስብቻ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ ስዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ አበባ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን አልማ ህንፃ 2ኛ ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 551 2528 /በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

Tender details

  • Deadline: 2026-05-22
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-22 15:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amhara Universal Development Association
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 13, 2026
  • Posted at: 2026-05-13T11:06:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders