የአማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን የልማትና ተራድኦ ማኅበር (EUCDRA) ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎችን አወዳድሮ የእርዳታ ዕህሎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡01/2026

የአማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን የልማትና ተራድኦ ማኅበር (EUCDRA) ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎችን አወዳድሮ የእርዳታ ዕህሎችን ለመግዛት ይፈልጋል።

የአማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን የልማትና ተራድኦ ማኅበር ከ ሲአይኢ ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በአጽቢ ከተማ ለተጎዱ ወገኖች የምግብ እና የስነ-ምግብ እቃዎችን በማቅረብ ሰብዓዊ ድጋፍ መስጠት ይፈልጋል። እናም ለዚህ ዓላማ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የእርዳታ አይነቶች ለማቅረብ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ተጫራቾችን ይፈልጋል።

ተጫራቾች በኢትዮጵያ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2018 እና ከዚህ ጋር ተያያዥ መመሪያዎች መሠረት በሚያቀርቡት እቃ ዘርፍ የተመዘገቡ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የTIN ሰርተፍኬት፣ የ2018 ዓ/ም የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እና ሌሎች ተዛማጅ ህጋዊ መስፈርቶች ያላቸው መሆን አለባቸው።

EUCDRA ለእርዳታ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልጋቸው የምግብ እና የስነ ምግብ አይነቶች ዝርዝር ፦

ተ.ቁ

የአቅርቦት አይነት

ብዛት በኪግራም/ በሊትር

መዳረሻ ቦታ

1

1ኛ ደረጃ በቆሎ

 

ትግራይ ክልል አጽቢተማ

2

1ኛ ደረጃ ሽንብራ

 

ትግራይ ክልል አጽቢተማ

3

ፈሳሽ የምግብ ዘይት

 

ትግራይ ክልል አጽቢተማ

4

ፋፋ አልሚ ምግብ

 

ትግራይ ክልል አጽቢተማ

 

ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ማለትም ከግንቦት 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 12/2018 የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚወዳደሩበትን እቃ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ዶክመንት ለሁሉም ዕቃ በ2,000 ብር በመግዛት ሁሉንም ህጋዊ ሰነዶች ከእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ጋር ለእያንዳንዱ እቃ ለየብቻለአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ልማትና ተራድኦ ማኅበር አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ

  • ጨረታው በማግስቱ ግንቦት 13/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች በተገኙበት በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል።
  • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች ዋጋቸውን ሲያቀርቡ የመድረሻ ቦታውን የአጽቢ ከተማን እርቀት እንዲያጤኑ ይመከራል።

አድራሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ መካኒሳ/ቆሬ ኮንዶሚኒየም አካባቢ፣ ከመካኒሳ ወደ ቆሬ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ኮንሶላታ የካቶሊክ ገዳም ፊትለፊት 50 ሜትር ገባ ብሎ። ስልክ ቁጥር 09 70–57-30-30፣ 09-61-24-65-70

አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን የልማትና ተራድኦ ማኅበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-20
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid opening: 2026-05-21 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amanuel Union Church Development and Development Association
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 2,000 ብር
  • Published: May 14, 2026
  • Posted at: 2026-05-14T09:04:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders