የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት የተለያዩ ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 መሠረት ተረክቦ ሁለት ጊዜ ሐራጅ ወጥቶ ሳይሸጥ የቀረውንና ባንኩ በቋሚነት የተረከበውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ እጅ በእጅ/በካሽ/ወይም በከፊል ብድር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

 የተበዳሪው /የመያዣ ሰጪው/ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የመያዣ ንብረት ዝርዘር መረጃ

ቀሪ የመሬት ሊዝ ውል (በዓመት)

የጨረታው መነሻ ዋጋ (ብር)

የጨረታው ደረጃ

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት

1

ኤም. ኤ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ እርሻ ልማት ድርጅት

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት አኙዋ ዞን፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ሶለን ቀበሌ

500 ሄክታር የእርሻ መሬት (390 ሄክታር የለማ)።

38

33,047,344.67

ዝግ ጨረታ (1ኛ)

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ  ዲስትሪክት  ጽ/ቤት፣ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት

 

 

መጋዘን፣ ቢሮ፣ የሠራተኛ መኖሪያ፣ ካፌቴሪያና ሌሎች ግንባታዎች።

የእርሻ መሣሪያዎች (ANDIN ትራክተሮች ሞዴል  DT100 እና DT125፤ የተመረተበት ዘመን 2014 እና 2015)።

ተሽከርካሪዎች (SUZU የጭነት መኪና እና TOYOTA ባለ ሁለት ጋቢና ፒክ-አፕ፤ የተመረተበት ዘመን 2014 እና 2015)።

 የጨረታው መመሪያ፦

  1. በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ፈቃድ፣ የቲን (TIN) ቁጥር እና በሕግ የተረጋገጠ ውክልና እንዲሁም ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) በማቅረብ መሳተፍ ይችላሉ።

3. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ይጽፋል።

4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

5. በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

6. አሸናፊው 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችንና ሌሎች ሕጋዊ ወጪዎችን ይሸፍናል።

7. ባንኩ ባለው የብድር ፖሊሲ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ አሸናፊዎች በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።

8. ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር መጎብኘት ይችላሉ።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 47 551 2577 / +251 47 551 2588 / +251 47 151 8284 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-12 10:00
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 14, 2026
  • Posted at: 2026-05-14T09:12:13.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders