የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ የወንዶች እና ጉርድ ጫማ እንዲሁም የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ የወንዶች እና ጉርድ ጫማ እንዲሁም የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

1. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ ብር 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው።

5. የቴክኒካል ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ ሰነድ 7/9/2018 ቀን እስከ 21/9/18 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

7. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 22/9/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል።

8. ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 025 111-7455 / 025 111-3743 በመደወል ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-05-30 09:30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Police Commission
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 15, 2026
  • Posted at: 2026-05-15T07:49:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders