በሀድያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ላብራቶሪ ማሽን (CBC) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀድያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የህክምና ዕቃዎች ግዥ በአገር አቀፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

1. የላብራቶሪ ማሽን (CBC) ግዥ

የጨረታ መመሪያ

  • ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ ግብር ከፋይነት ማስረጃ የዘመኑ ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ በመንግስት ግዥ ላይ መሳተፍ የሚችሉበት የአቅራቢነት ማስረጃ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ህንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከጧት 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በሆሳዕና ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ ቤት በመክፈል ባለፍቃዱ ወይም ህጋዊ ወኪል ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ የሠነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናCPO/፡1ኛ.የጨረታማስከበሪያ ዋስትና 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) የቀረበ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ማቅረብ ይጠበቅበታል፣_
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል፣ ሁለት ፎቶ ኮፒ፣ የተፈረመና ቀን ያለበት የጨረታ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ሞልቶ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/፣ እያንዳንዱን በፖስታ በማሸግ በመጨራሻም በአንድ በሰም በታሽገ እናት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ የአጫራች መስሪያ ቤት ስም፤ የዕቃ ስም እና የአቅራቢ ድርጅት ስም በፖስታው ላይ በመጻፍ፣ የአቅራቢ ድርጅቱን ማህተም በፖስታው ማሳረፍ፣በፖስታው ላይ ኃላፊነት በተሰጠው አካል በመፈረም በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ህንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 አራተኛ ፎቅ ላይ  ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  • በእጅ የተሞላ ኮፒ ሰነዶችን እንደ ኦርጅናል ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የጨረታ ዋጋ በሰነድ ላይ በተዘጋጀ ቦታ ብቻ መሞላት አለበት
  • ሁሉም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍና መፈረም አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ከጨረታ ሂደት ውጪ ያደርጋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ሰነድ ላይ አንድ ሐሰተኛ እና የተጭበረበረ ሰነድ ቢገኝ ከጨረታ ሂደት ውጪ ከተደረገ በኃላ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
  •  በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ቅሬታውን በጽሁፍ ለመስሪያ ቤቱ ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 001 ማቅረብ ይኖርበታል!
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖርም።
  • ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የውክልናውን ኦርጅናል ይዞ ሊቀርቡ ይሆናል፣
  • ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ተጫራች አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ 0465551841/0916838549
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-25
  • Publishing entity: Hosana City Administration Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders