የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የፈረንጅ ጽድ ግንዲላና የጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የፈረንጅ ጽድ ግንዲላና የጣውላ የምርት ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት እንጅባራ ቅ/ጽ/ቤት ፋግታ ለኮማ ወረዳ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ የተመረተ የፈረንጅ ጽድ ግንዲላ የምርት መጠኑ 686.66 ሜ/ኩብ እና ደማርቆስ ቅ/ጽ/ቤት እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ የጣውላ ምርት 62.56 ሜ/ኩብ ፣ ደ/ታቦር ቅ/ጽ/ቤት እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ የጣውላ ምርት 29.02 ሜ/ኩብ እና እንጅባራ ቅ/ጽ/ቤት እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ 153.54 ሜ/ኩብ በድምሩ 245.12 ሜ/ኩብ የጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች -
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ የቀረቡትን የጣውላ ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ፣ደ/ታቦር ፣ደ/ማርቆስ ፣ እንጅባራና ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመናዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መሣዛት የሚፈልጉትን ምርት በአሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያ ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06'ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፈ/ጽድ ግንዲላ እና የጣውላ ምርት ሽያጭ ማስታወቂያ››ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ አስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
- ተጫራቾች የሚፈልጉትን ሎት ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑንና የተወዳደሩበትን ሎት የጣውላ ምርት ሁሉንም ምርት ክፍያ ፈፅመው ማንሳት አለባቸው፡፡
- ደንበኛው ከአሁን በፊት ምርት ገዝቶ ክፍያ ያላጠቃለለ ከሆነ ክፍያ እስከሚጨርስ ድረስ ሌላ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም :
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095 ደ/ታቦር 0584410306፣ደ/ብርሃን 0116375017 እንጅባራ 0582270485፣ ደ/ማርቆስ 0588719004 ኮ/ቻ 0914716636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-05-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ አስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-26 10:15
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ አስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Forest Enterprise
- Buyer address: ባህር ዳር ቀበሌ 14 አረጋውያን ህንፃ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 15, 2026
- Posted at: 2026-05-15T08:08:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.