የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ስኳር እና የተለያዩ ዕቃዎችን ማሽነሪዎችን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች እንዲጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/22/SIG/2018
1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ለ2018/19 በጀት ዓመት ስኳር እና የተለያዩ ዕቃዎችን ማሽነሪዎችን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች እንዲጓጓዝልት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ጥቅል ሎት 1 የስኳር ምርት ከፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዝ እና
- ጥቅል/ሎት:2 የተለያዩ ዕቃዎችን ማሽነሪዎችን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ማጓጓዝ
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ሕጋዊ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ) የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ብቁ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 551 6271/500417፣
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡15 ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት፡ 1 ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ለሎት፡2 ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል።
8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-05-25 14:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
- Buyer address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 15, 2026
- Posted at: 2026-05-15T08:30:48.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.