በደ/ኢ/ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ በዲላ ከተማ የተማሪዎች ማደሪያ ግንባታ ሥራን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ኢ/ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ በዲላ ከተማ የተማሪዎች ማደሪያ ግንባታ ሥራን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1. ደረጃቸው BC 5/GC 5 እና ከዛ በላይ የሆኑ

2. ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2018 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣

3. ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በተቋሙ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 1,000,000 /አንድ ሚሊዮን ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም ባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው::

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎኘ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ/ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ተቋሙ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው::

6. ጨረታው በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

8. ተቋሙ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደ/ኢ/ክ/መንግስት ባወጣው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በመመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል።

ለበለጠ ማብራሪያ፡-

በስልክ ቁጥር፦ 0463313624/0463314251

በደ/ኢ/ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-15 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Dilla Education College
  • Bid bond: 1,000,000 /አንድ ሚሊዮን ብር/
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: May 15, 2026
  • Posted at: 2026-05-15T08:32:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders