የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጉራጌ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ ሲሆን ኮሌጁ የጋርመንት እና የሰብል ልማት ማሰልጠኛ ህንጻዎች ግንባታ ስራ ለማከናወን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ አ/ፖ/ቴ/ኮ/03/2018
የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ጉራጌ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ፖለቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ ሲሆን ኮሌጁ የጋርመንት እና የሰብል ልማት ማሰልጠኛ ህንጻዎች ግንባታ ስራ ለማከናወን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በደረጃው ቢሲ-5 ጂሲ 5 እና ከዚህ በላይ ፍቃድ ያላቸው፣
3. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፤
5. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፤
6. ተጫራቾች ከላይ የተገለፁት መስፈርት አሟልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 21ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
7. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ
ሀ) ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 / አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የጨረታ ማስከበሪያዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሽግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት፤
ለ) ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሽግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ /ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
8. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስም እና ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።
9. ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፤
10. የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
11. የፋይናንሺያል (የፕሮጀክቱ ግንባታ ዋጋ/ ከቴክኒክ ግምገማ ውጤት በሗላ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉት ተጫራቾች ሰነድ ብቻ የጨረታው ኮሚቴው በማስታወቂያ በሚገለፀው ቀን ይከፈታል፤
12. መስሪያቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ፤
ማሳሰቢያ፡-
1ኛ/ የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምረያ ከሚከታተላቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ በአፈፃፀማቸው ምክንያት 3 ዙር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ውል ያቋረጡ ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም፤
2ኛ/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፤
3ኛ) በጨረታው ሂደት ውስጥ ተሻሽሎ የወጣው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግዢ መመሪያ/2018 ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልፃለን፤
የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Publishing entity: አገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
- Bid bond: 150,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 15, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.