ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ /Deep Well Drilling Project/ ተቋራጮችን ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ / Deep Well Drilling Project/
ቦታ፦ በደብረ ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ፣ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ፣ ቦራሌ ቱሉ አምባ እና ጠንቆሌ የገጠር ንዑስ ቀበሌ።
ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ዙሪያ በሚገኙ 4 የፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የ4 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ ግንባታ እና የውሃ ምርታማነት ሙከራ ሥራዎችን ብቃት ባላቸው ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል።
- ለመፅደቅ ሳይት፦ 1 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ (ከ160-180 ሜትር)።
- የቦራሌ፣ የጠንቆሌ እና የቱሉ አምባ መንደሮች፦ 3 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች (ከ140-160 ሜትር)።
ተጫራቾች ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የሚከተሉትን ሕጋዊ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑ የግብር ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰነድ።
- ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የደረጃ 5 (WWC/WWD-5) እና ከዚያ በላይ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት።
- በመንግሥት የጨረታ እገዳ (Debarment) ውስጥ ያልተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 13 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ጨምሮ ) ዘወትር በሥራ ሰዓት መተው የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ13ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት ታሽጎ፣ በዚያው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡ አያት ዞን አምስት መንገድ 14
+251 97 657 2397/ +251 91 361 0673
tojustify24@gmail.com / info@alemetsdek.com
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ13ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-27 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ13ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ለመጽደቅ ዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 15, 2026
- Posted at: 2026-05-15T08:56:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.