የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የስቱዱዮ ወንበርና ሶፋ እና የስቱዱዮ ኒውስ ቴብል እና ፖዲየም መግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ NCB 004/2018

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የቀረበውን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ NCB 004/2018 አወዳድሮ የስቱዱዮ 2 እና ስቱዱዮ 3 ፈርኒቸር መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የስቱዱዮ ወንበርና ሶፋ
  • ሎት 2 የስቱዱዮ ኒውስ ቴብል እና ፖዲየም

በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ቲን ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

3.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቴክኒካልና ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በኢንቨሎፕ በማድረግ መቅረብ አለበት። የኮፒ ሰነዶች ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር በአይነትም ሆነ በብዛት ተመሳሳይ መሆን አለበት።የጨረታውን ስምና ቁጥር በመግለጽ በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው (ለሁለቱም ሎቶች) በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል።

6. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር /011-517-2521/11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-05 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡45 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Broadcasting Corporation
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 16, 2026
  • Posted at: 2026-05-16T07:39:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders