በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች የማስታወቂያ(የፕሮሞሽን ዕቃዎች)፣ የኤሌክትሪካል ወርክ ሾፕ መካኒካል ወርክ ሾፕ ዕቃዎች፣ ለካፌ አገልግሎት የሚውሉ ወንበሮች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የ.ጨ.ሰ.ቁ.:- NCB- AAMMI-005/2018

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተለያዩ አገልግሎቶች የማስታወቂያ(የፕሮሞሽን ዕቃዎች)፤ የኤሌክትሪካል ወርክ ሾፕ መካኒካል ወርክ ሾፕ ዕቃዎች፤ ለካፌ አገልግሎት የሚውሉ ወንበሮች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት-1፡-የፕሮሞሽን ህትመቶችና ዕቃዎች
  • ሎት-2፡-የኤሌክትሪካል ወርክ ሾፕ እና መካኒካል ወርክ ሾፕ ዕቃዎች
  • ሎት-3፡- ለካፌ አገልግሎት የሚውሉ ወንበሮች
  • ሎት-4፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

 

  • በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ /ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ/የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  • ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።

(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣

(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣

  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር የስራ ቀን) ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከረፋዱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም።
  • ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022 111 0689/ 09 12 26 46 80 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡-አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500ሜ ላይ
ስልክ:- 022 111 0689/ 09 12 26 46 80 ፋክስ:-022 111 1866
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩኘ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-27 14:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Agricultural Machinery Processing Industry
  • Buyer address: አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500ሜ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T07:52:50.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders