በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ/ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የካፒታል በጀት እና SEED (ሲድ) ከተባለ ግብረ - ሠናይ ድርጅት በተመደበለት በጀት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለአጫጭር ጊዜ ሥልጠና አገልግሎት የሚውል ቋሚ የሥልጠና መሣሪያ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴከኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በ2018ዓ/ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የካፒታል በጀት እና SEED (ሲድ) ከተባለ ግብረ - ሠናይ ድርጅት በተመደበለት በጀት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለአጫጭር ጊዜ ሥልጠና አገልግሎት የሚውል ቋሚ የሥልጠና መሣሪያ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛቹኋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ያላትና፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ፣ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት/፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች የቲን ቁጥር /tin Number/ ያለው /ያላት
2. በመንግሥት ግዥ አቅርቦት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
3. የዕቃውን ዋጋ በኮሌጁ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ገፁን ሳይገነጣጥል ሞልቶ የሚያቀርብ
4. የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ የዕቃዎች መለያ / specification/ ኮሌጁ ባዘጋጀው መሠረት ብቻ የሚያቀርብ/የምታቀርብ ፣
5. የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ /CPO/ ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ጋር በማሸግ ማቅረብና ማስያዝ ይገባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን / Bid Document/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአ/ም/ጭ/ ፖ/ቴ/ሳ/ ኢንስቲትዩት ክ/ሂ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200፡00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን፣ ማህተምና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
9. አጠቃላይ የማስረጃቸውን ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል የሚል ማህተም አርፎበት እና ተፈርሞበት ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
10. የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሰነድ በሁለት ኮፒ ተዘጋጅቶ የዕቃው ነጠላ ዋጋ በአንድ ላይ በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ቀን የሚያበቃው የሥራ ቀን ከሆነ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የታሸገው ሣጥን በአ/ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ሳታላይት ኢንስቲትዩት በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል ቀኑ በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል
11. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም። እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ውጪ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም።
12. አሸናፊዎች የዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ውል መፈራረም አለባቸው፣፣
13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብና ማስረከብ አለበት።
14. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ " ወይም በከፊል የመሰረ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. የተጭበረበረ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም በሕግም ያስቀጣል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 046 881 0960 / 09 10 74 41 29 / 09 12 05 69 62
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-02 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛ ቀጥሎ ባለው ቀን ቀን ልክ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Arba Minch Poly Technic & Satellite Institute
- Bid bond: 5,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T08:23:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.