የደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ልዩ ልዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሽያጭ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ልዩ ልዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለገ ማንኛውም ተጫራቾ፣

1. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር በማያያዝ ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፣ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ወይም በባንክ የተረጋገጠ cpo መሆን ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር አይነትና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ እዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 300/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል።

5. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዋጋ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

6. አሸናፊ ተጨራቾች የአሸናፉበትን ገንዘብ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቶቹን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካላነሱ የጨረታ ማስከበሪያው ተወርሶ ኮሌጁ የተሻለውን ሌላ አማራጭ ሊወስድ ይችላል።

7. ተጫራቾች የእቃውን ሁኔታ በስራ ሰዓት በኮሌጁ መጋዘን ድረስ በመቅረብ ማየት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

9. ተጫራቹ በጨረታው የአሸነፉባቸውን እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10/100 ውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ደረሰኝ / cpo ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

ስልክ ቁጥር 0116 815 616 / 0116 812 572/12

ደ/ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-01 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debre Berhan Poly Technic Collage
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T08:29:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders