Construction machinery and equipment rental

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 10 ቶን ሃፍ ክሬን እና ባለ 40 ጫማ ሃይቤድ ከባድ ጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/11/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የኪራይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  • ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEP Transmission Substation Construction Account No. 1000252665203 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-19 ትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 114 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን የኪራይ አገልግሎቶች በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/11/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የኪራይ አገልግሎቶች ግዥ መወዳደር ይችላሉ።

የአገልግሎት ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የጨረታው መዝያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

ባለ 10 ቶን ሃፍ ክሬን እና ባለ 40 ጫማ ሃይቤድ ከባድ ጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ

ብር 100,000.00

ግንቦት 25 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት

ግንቦት 25 ቀን 2018 . ከቀኑ 815 ሰዓት

  • ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 673 2190 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-02 14:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (May 17, 2026)
  • Posted at: 2026-05-18T08:38:05.000Z
← Back to all tenders