የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት: ሁለተኛ ዙር የወጣ የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

Description

ሁለተኛ ዙር የወጣ የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት በቁጥር 241/228//2018 እና በቀን በ11/6/2018 ዓም በካምባ ከተማ በላገፉ ቀበሌ ልዩ ስም የለለ ደን የሚባል ቦታ የሚገኘዉ የለማ የመንግስት ደን ከዋናዉ አስፓልት መንገድ እስከ የለለ ችግኝ ጣቢያ ድረስ 300 ሜትር መኪና የምያስገባ ጠጠር መንገድ ሲሆን ከችግኝ ጣቢያዉ እስከ መጨረሻ ደኑ ድረስ 800 ሜትር መንገድ መኪና የማይገባ መሆኑን ገልጾ ካምባ ከተማ አስር በፃፉት ደብዳቤ መሠረት ካምባ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላላቸዉ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት የሚከተሉትን የመወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡-

  • የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሴርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ህጋዊ ሰዉነት ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
  • የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  • ለጨረታ የቀረበዉን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀዉ የመጫረቻ ሠነድ ላይ በተገለፀዉ ቦታ ድረስ በመሄድ የጉልበት ዋጋን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ጨረታዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ሥራ ቀናት ማየት ይችላል።
  • የተዘጋጀዉን የመጫረቻ ሠነድ ካምባ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋ/ሥ ሂደት ቢሮ ቁጥር≠3 በመገኘት ብር 300 / ሶስት መቶ ብር ብቻ ከፍሎ በሥራ ቀናት መግዛት ይችላል።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን ዓይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ /በባንክ ማዘዣ(CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች መግዛት የሚፈለጉት የእያንዳንዱ የደን ዓይነትና መጠን እና የሚገዙበትን ዋጋ ከሰማቸዉና ከአድራሻቸዉ ጋር በተናጠል በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ የደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት የጋሞ ዞን በካምባ ከተማ አስ/ር የመንግስት ደን ጨረታ ተብሎ በጉልህ ከተጻፈበት በኋላ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 20ኛዉ ቀን 11 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል።
  • ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር 20ኛዉ ቀን 11 ሰዓት ላይ ካምባ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር≠3 ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሣጥን ጨረታዉ ይዘጋል በ21ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡45 ሰዓት ላይ ሕጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፤ ባይገኙም የጨረታዉ ሂደት አይስተጓገልም።
  • የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓላት ቀን የሚዉል ከሆነ ስራዉ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ላይ ይፈጸማል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 71 00 65/ 09 16 85 53 56/ 09 16 60 00 27/ ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ
ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር 20ኛዉ ቀን 11 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-10 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡45 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 16, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T08:46:17.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders