Well drilling and boreholes

ለመጽደቅ የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ ግንባታ እና የውሃ ምርታማነት ሙከራ ስራዎችን ብቃት ባላቸው ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ/ Deep Well Drilling Project/

ቦታ፦ በደብረ ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክፍለከተማ፣ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ፣ ቦራሌ ቱሉ አምባ እና ጠንቆሌ የገጠር ንዑስ ቀበሌ ለመጽደቅ የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ዙሪያ በሚገኙ 4 የፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የ4 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ ግንባታ እና የውሃ ምርታማነት ሙከራ ስራዎችን ብቃት ባላቸው ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል።

  • ለመፅደቅ ሳይት፦ 1 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ (ከ160-180 ሜትር)።
  • የቦራሌ፣ የጠንቆሌ እና የቱሉ አምባ መንደሮች፦ 3 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች (ከ140-160 ሜትር)።

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የሚከተሉትን ህጋዊ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፦

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የዘመኑ የግብር ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ስነድ
  • ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የደረጃ 5 (WWC/WWD-5) እና ከዚያ በላይ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት።
  • በመንግስት የጨረታ እገዳ (Debarment) ውስጥ ያልተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ጨምሮ ) ዘወትር በስራ ሰዓት መተው የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት ታሽጎ፣ በዛው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡ አያት ዞን አምስት መንገድ 14
+251 97 657 2397 / +251 91 361 0673 [email protected]  / [email protected]  አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-29 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ለመጽደቅ ዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (May 17, 2026)
  • Posted at: 2026-05-18T11:00:57.000Z
← Back to all tenders